ሠራተኞችህ እስከ መጨረሻ የሚማሩት የእንግሊዝኛ ኮርስ።
በTutoro እያንዳንዱ ሠራተኛህ የራሱን የAI እንግሊዝኛ መምህር ያገኛል። ትምህርቶቹ ከግል አስተማሪ ጋር እንደመማር ጥራት አላቸው፣ በየቀኑም ለመመለስ ያጓጓሉ።
ጀምር
ማሳያ ለማየት ቀጠሮ ያዝ
ለእያንዳንዱ ሠራተኛ በወር ከ$9 ጀምሮ። በፈለግኸው ጊዜ ምዝገባህን ሰርዝ።
Tutoro እንዴት ይሠራል? · 2 ደቂቃ
እንዴት እንደሚሠራ እይ
ቪዲዮውን ዝጋ
አዲስ ደረጃ!
A1 → A2
+ 138 XP
እስካሁን ከሁሉ የተሻለው ቀን
በአንድ ለአንድ ውድድር አሸነፍክ
በዙር ብዛት 3 ለ1
የዛሬን ተግባሮች ጨርሰሃል
3 / 3
የ30 ቀናት Streak
አንድም ቀን ሳያመልጥ
+ 250 ሳንቲሞች
የሳምንቱ ጉርሻ
አዲስ ደረጃ!
A2 → B1
በሊጉ አንደኛ
ከ30 ተወዳዳሪዎች 1ኛ
አዲስ አስተማሪ አገኘህ
Katie
ሁሉም ትክክል!
ከ12 ጥያቄዎች 12 ትክክል
የትምህርት ክፍሉን ጨርሰሃል!
ጉዞ
የመጀመሪያው ሙሉ ዓረፍተ ነገር
ድምፅህን አሰምተህ ተናገርክ
አምስት ትምህርቶች በተከታታይ
በአንድ ጊዜ
አዲስ ልብስ አገኘህ
5 000 አወጣህ
አዲስ ደረጃ!
B1 → B2
የመናገር ችሎታ ፈተናውን አለፍክ
በሁለተኛው ሙከራ
ኩባንያዎች ይተማመኑብናል
500
+
ኩባንያዎች
ሠራተኞቻቸውን በTutoro ያስተምራሉ
1M
+
ሠራተኞች
በየቀኑ ይማራሉ
87
%
ንቁ ተጠቃሚዎች
ከ90 ቀናት በኋላም መለማመዳቸውን ይቀጥላሉ
Northbeam
ALTAVIA
Quadra
helioworks
Verado
ኩባንያህ ከTutoro ምን ያገኛል?
በቀን 15 ደቂቃ በስልክ መማር ብቻ። የክፍል ጊዜ ማስተካከል አያስፈልግም። ይህ ለኩባንያህ ምን እንደሚያመጣ ተመልከት።
በእንግሊዝኛህ የንግድ ስምምነቶችን አሳካ
49% የሚሆኑ ኃላፊዎች አለመግባባት ዓለም አቀፍ የንግድ ስምምነት እንዳከሸፈባቸው ይናገራሉ። Tutoro የሠራተኞችህን እንግሊዝኛ ያሻሽላል፣ ከግል አስተማሪ እስከ 50 እጥፍ ባነሰ ወጪ።
ሠራተኞችህ ሳያቋርጡ የሚከታተሉት ስልጠና
እንግሊዝኛ የመናገር ችሎታን በማሻሻል AI ከመምህራን የተሻለ ውጤት አስመዝግቧል። Tutoro ልምምዱን የዕለት ተዕለት ልማድ ያደርገዋል፤ ትምህርቱን ከጨዋታ ጋር ማዋሃዱም 88% የሚሆኑት ሠራተኞች በበለጠ ደስታ እንዲማሩ ያደርጋል።
ሠራተኞችህን አብቃ፣ የቅጥር ወጪህን ቀንስ
መማርን ባህል ባደረጉ ድርጅቶች የሠራተኞች የመቆየት መጠን በ57% ይበልጣል። በድርጅቱ ውስጥ ወደ ሌላ የሥራ ድርሻ የሚሸጋገሩትም በ23% ይበልጣሉ። ስለዚህ ከውጭ አዲስ ሰው መቅጠር የሚያስፈልግህ አነስ ይላል።
ከሌሎች አማራጮች ጋር ሲነጻጸር
Tutoro በምን ይሻላል?
ሠራተኞችህ በሚመቻቸው ጊዜ ይማራሉ። አንተም ለአስተዳደር የምታወጣው ጊዜ ያንሳል፣ ወጪህንም አስቀድመህ ታቅዳለህ።
ዋጋው እንደ ምዝገባ አማራጩና እንደ ሠራተኞች ብዛት ይለያያል
የቡድን ትምህርት
የግል አስተማሪ
Tutoro
ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የሚወጣ ወጪ
በወር ከ$180 እስከ $320
በሰዓት ከ$40 እስከ $120
በወር ከ$9 ጀምሮ
የትምህርት መርሐ ግብር
ቋሚ የትምህርት ሰዓት
አስቀድመህ የትምህርት ቀጠሮ መያዝ አለብህ
በሚመችህ ጊዜ ተማር። 15 ደቂቃ ብቻ ቢኖርህም በቂ ነው።
ለእያንዳንዱ የሚስማማ ትምህርትና ማበረታቻ
ሁሉም በተመሳሳይ ፍጥነት ይማራሉ፣ የጨዋታ እንቅስቃሴዎችም ጥቂት ናቸው
ትምህርቱን ለፍላጎትህ ማበጀት በአስተማሪው ይወሰናል
ከእያንዳንዱ ሠራተኛ ደረጃና ግብ ጋር ይስማማል፣ ጨዋታዎቹም የመማር ፍላጎታቸውን ያነቃቃሉ
ለሰው ኃይል ክፍል የእድገት መረጃ
የክፍል ተሳትፎ ሪፖርት
የሰው ኃይል ክፍሉ እድገትን ለመከታተል በቂ መረጃ አያገኝም
ወቅታዊ መረጃ የሚያሳይ ዳሽቦርድ + የእድገት ሪፖርቶች
ትምህርቱን ለሁሉም ሠራተኞች ማዳረስ
ቡድኖች ሲበዙ ማስተባበሩ ይከብዳል
አዲስ ሠራተኛ በተጨመረ ቁጥር ወጪውና የማስተዳደር ሥራው ይጨምራሉ
ሁሉንም ሠራተኞችህን በትምህርቱ በቀላሉ አካትት
ለመጀመር
እንዴት ይሠራል?
ለሠራተኞችህ ምዝገባ ራስህ ግዛና ጋብዛቸው። በዚያው ከሰዓት ሁሉም መለማመድ ይጀምራሉ።
የተሳታፊዎችን ብዛት ምረጥ
የሠራተኞችን ብዛትና የምዝገባውን ቆይታ ምረጥ።
ሠራተኞችህን ጋብዝ
የኢሜይል አድራሻዎችን ዝርዝር ቀድተህ ለጥፍ፣ ወይም አንድ የመመዝገቢያ ሊንክ ለሁሉም ላክ።
እንግሊዝኛ መናገር ይጀምራሉ
ሠራተኞችህ ሊንኩን አንዴ ሲነኩ የመጀመሪያ ትምህርታቸውን ወዲያውኑ ይጀምራሉ።
እድገታቸውን ተከታተል
Streak፣ ሳምንታዊ እንቅስቃሴና የደረጃ ለውጥ፣ ሁሉንም በአንድ ማያ ገጽ ተከታተል።
የመማር ቀጣይነት
ሠራተኞች ለምን መማር ይቀጥላሉ?
ድምፅህን አውጥተህ የምትማርበት እውነተኛ ትምህርት
አንተ ትናገራለህ። መምህርህ ይመልሳል፣ ያብራራል፣ በውይይቱ መሃልም ልምምዶችን ይሰጥሃል።
ለማንኛውም ሁኔታ ተለማመድ
የሥራ ቃለ መጠይቅን ወይም ከሐኪም ጋር መነጋገርን ተለማመድ፣ በጀብዱ ታሪክ ውስጥ ተሳተፍ፣ ወይም የራስህን ሁኔታ ፍጠር።
ከማን ጋር ማውራት እንደምትፈልግ ምረጥ
የተለያየ አነጋገርና ባህሪ ያላቸው መምህራን አሉ። አብረኸው ለማውራት የሚመችህን ምረጥ።
ምን ማሻሻል እንዳለብህ በግልጽ እወቅ
ከእያንዳንዱ ትምህርት በኋላ ውጤትህን ተመልከት። የምትደጋግማቸውንም ስህተቶች እወቅ።
የማትረሳቸው ቃላት
ልትረሳቸው የቀረቡ ቃላትን በደንብ እስክታስታውሳቸው ድረስ በአጫጭር ጨዋታዎች ደጋግመህ ትለማመዳቸዋለህ።
የመማሪያ መንገድ፣ ማለቂያ የሌለው ይዘት ሳይሆን
በእያንዳንዱ ትምህርት በካርታው ላይ ወደፊት ትሄዳለህ፣ አንዱን ዓለም ስታጠናቅቅም የሚቀጥለው ይከፈትልሃል።
እውቀትህንም ደረጃህንም አሳድግ
የራስህን ገጸ ባህሪ ፍጠር። በእያንዳንዱ ትምህርት ደረጃው እያደገ በሊጎች ውስጥ ወደ ላይ ይወጣል።
ለሰው ኃይል ክፍል
ሠራተኞችህ እየተማሩ መሆናቸውን ለማወቅ መገመት አያስፈልግህም
ማን እንደሚማር፣ እንዴት እየተሻሻለ እንደሆነና የእያንዳንዱ ሠራተኛ የእንግሊዝኛ ደረጃ ምን እንደሆነ በአንድ ዳሽቦርድ ታያለህ። መረጃ ለማግኘት ሁሉንም እየዞርክ መጠየቅ ቀረ።
የሠራተኞች እንቅስቃሴ
ያለፉት 30 ቀናት · የናሙና መረጃ
ጥቅም ላይ ያሉ ፈቃዶች
ምዝገባ ከገዛህላቸው ሠራተኞች ስንቶቹ በየሳምንቱ እንደሚጠቀሙ እይ
የእያንዳንዱ ሠራተኛ የእንግሊዝኛ ደረጃ
በCEFR መለኪያ ከA1 እስከ C1። እየተማሩ ሲሄዱ የደረጃቸው መረጃም ይዘምናል።
የእያንዳንዱ ሠራተኛ የመማር እንቅስቃሴ
በሳምንት የተማሩባቸው ደቂቃዎች፣ ያጠናቀቋቸው ትምህርቶች እና Streak
ለፋይናንስ ክፍል ሪፖርቶች በማንኛውም ጊዜ
በማያ ገጹ የምታየውን መረጃ እንዳለ በCSV አውርድ።
Tutoro ለማን ይስማማል?
እንግሊዝኛህን ትንሽ ማሻሻል ዕለታዊ ሥራህን በእጅጉ ሊያቀልልልህ ለሚችልባቸው የሥራ ዘርፎች።
ጀምር
የደንበኛ ድጋፍ ቡድኖች
ሽያጭ
ምህንድስና
ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች
የችርቻሮ ንግድ
የጤና አገልግሎት
ማርኬቲንግ
የስኬት ታሪኮች
በሦስት ኩባንያዎች ምን ተለወጠ?
ቀድሞ ሠራተኞቻችን የእንግሊዝኛ ትምህርታቸውን በፍላጎት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይከብደን ነበር። ከTutoro ጋር ግን ተደስተው ይማራሉ፣ አያቋርጡም። ድርጅቱ እንደሰጣቸው ጠቃሚ ተጨማሪ ጥቅምም ያዩታል። የሠራተኞቻችን እርካታ ጨምሯል።
የሰው ኃይል ኃላፊ
Northbeam
የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞቻችን አሁን የውጭ አገር ደንበኞችን በበለጠ መተማመን ያገለግላሉ። ጉዳዮችን ለኃላፊዎቻቸው ማስተላለፍም ቀንሰዋል። በግልጽ ይግባባሉ፣ ብዙ ጉዳዮችን በራሳቸው ይፈታሉ። ደንበኞቻችንም የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ።
የደንበኛ ድጋፍ ኃላፊ
Altavia
አሁን ለሥልጠና የምናወጣው ገንዘብ ምን ውጤት እያመጣ እንደሆነ በግልጽ እናያለን። የTutoro ትንታኔዎች ማን እየተማረ እንደሆነ፣ ምን ያህል እንደተሻሻለና የት ላይ ተጨማሪ ልምምድ እንደሚያስፈልገው ያሳዩናል። አሁን ውሳኔዎቻችንን በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርተን እንወስናለን።
ዋና የኦፕሬሽን ኃላፊ
Helioworks
ዋጋዎች
በወር ለአንድ ሠራተኛ ከ$9 ጀምሮ
ስንት ሠራተኞች ይማራሉ?
ለሁሉም ሠራተኞችህ በአንድ የቅናሽ ዋጋ ትምህርት አቅርብ።
በወር ለእያንዳንዱ ሠራተኛ
ለቡድን ትምህርት የምታወጣው
ለግል አስተማሪ የምታወጣው
አብረን እናስላ
ከ1,000 በላይ ተማሪዎች ካሉህ፣ ለድርጅትህ የሚስማማ ዋጋ እናቀርባለን። እንደ ተማሪዎችህ ብዛት ቅናሽ ታገኛለህ፣ በክፍያ መጠየቂያም መክፈል ትችላለህ። የሽያጭ ቡድናችን ወጪውን ከአንተ ጋር ያሰላል።
ለማሳያ ቀጠሮ ያዝ
የደንበኝነት ጊዜ
ተማሪዎች
Tutoro፣ የአንተ ጥቅል
በፈለግኸው ጊዜ ሰርዝ
ስንት ሠራተኞች ይማራሉ?
በአንድ የቅናሽ ዋጋ፣ ሁሉም ሠራተኞችህ እየተዝናኑ መማራቸውን እንዲቀጥሉ አድርግ።
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
በኩባንያችን Tutoroን መጠቀም እንዴት እንጀምራለን?
የድርጅትህን መለያ ፍጠር፣ ስንት ሠራተኞች እንደሚማሩ ምረጥና ግብዣ ላክላቸው። እያንዳንዱ ለደረጃውና ለግቡ የሚስማማ የእንግሊዝኛ ትምህርት ያገኛል። መጀመሪያ Tutoro እንዴት እንደሚሠራ ማየት ትፈልጋለህ? ለማሳያ ቀጠሮ ያዝ።
Tutoro ስንት ያስከፍላል? እንዴትስ እከፍላለሁ?
የTutoro ዋጋ ለአንድ ሠራተኛ በወር ከ$9 ይጀምራል። ቢያንስ 5 ሠራተኞችን ማስመዝገብ ያስፈልጋል። በካርድ ክፈል፣ ወይም ከድርጅትህ የአስተዳደር ገጽ በቀጥታ የክፍያ መጠየቂያ አውጣ።
የአንድን ሠራተኛ ምዝገባ ለሌላ ሠራተኛ ማስተላለፍ እችላለሁ?
አዎ። አንድ ሠራተኛ ሥራ ሲለቅ ወይም መማር ሳያስፈልገው ሲቀር፣ የመማሪያ ቦታውን ለሌላ ሠራተኛ ስጥ። በዚህ መንገድ ሠራተኛ በቀየርክ ቁጥር አዲስ ቦታ መግዛት አያስፈልግህም።
በፈለግሁበት ጊዜ የተጠቃሚዎችን ብዛት መጨመር ወይም መቀነስ እችላለሁ?
እንደሚያስፈልግህ የመማሪያ ቦታዎችን ጨምር ወይም ቀንስ። ጠቅላላ ቁጥራቸው ግን ከ5 ማነስ የለበትም። ክፍያህ ምን ያህል እንደሚለወጥ የሚወስኑት የደንበኝነት ውልህ ሁኔታዎች ናቸው።
ሠራተኞች በTutoro ምን ይማራሉ?
እንግሊዝኛ ለመማር የሚያስፈልገውን ሁሉ በTutoro ታገኛለህ። ከAI አስተማሪ ጋር ተማር፣ መናገር፣ ማዳመጥና ማንበብ ተለማመድ። በተለያዩ መልመጃዎች ተሳተፍ፣ አጠራርህን አስፈትሽና ወዲያውኑ ምክርና እርማት አግኝ። ሁሉም በአንድ መተግበሪያ።
Tutoro ከእያንዳንዱ ሠራተኛ የእንግሊዝኛ ደረጃ ጋር ይጣጣማል?
አዎ። እያንዳንዱ ሠራተኛ ለደረጃውና ለግቦቹ የሚስማማ የትምህርት ዕቅድ ያገኛል። ጨዋታ የተቀላቀለባቸው መልመጃዎችም ፍላጎቱን ጠብቆ መማሩን እንዲቀጥል ያግዙታል።
ሠራተኞች በቀን ለመማር ምን ያህል ጊዜ ያስፈልጋቸዋል?
ሠራተኞችህ በተመቻቸው ጊዜ መማር ይችላሉ። ለአንድ ጊዜ ልምምድ 15 ደቂቃ እንኳን ይበቃል። የተወሰነ የክፍል ሰዓት የለም፣ ለትምህርት ቀጠሮ መያዝም አያስፈልግም።
Tutoro ሠራተኞች በጉጉት መማራቸውን እንዲቀጥሉ እንዴት ያበረታታል?
Tutoro ለእያንዳንዱ ሠራተኛ የሚስማሙ ትምህርቶችን፣ ጨዋታዎችን፣ ሽልማቶችንና በንቃት የሚሳተፉባቸውን ልምምዶች አንድ ላይ ያቀርባል። በዚህም ሠራተኞችህ በየቀኑ ለመማር ይጓጓሉ፣ ቀስ በቀስም ልማድ ያደርጉታል።
የሰው ኃይል ክፍል የእያንዳንዱን ሠራተኛ እድገት መከታተል ይችላል?
አዎ። በኩባንያህ ዳሽቦርድ ማን ምን ያህል ጊዜ እንደሚማርና ምን ያህል እንደተሻሻለ ማየት ትችላለህ። የሰው ኃይል ክፍሉም የሠራተኞችን ተሳትፎና እድገት በቀላሉ ይከታተላል።
ሠራተኞች የኩባንያ ኢሜይል አድራሻ ያስፈልጋቸዋል?
አያስፈልግም። የመጋበዣ ኮዱ ከኢሜይል አድራሻ ጋር አይታሰርም። ኮዱን የሚያስገባው ሰው የመማሪያ ቦታውን ያገኛል። ሠራተኛው ቀድሞውኑ Tutoro በግል መለያው የሚጠቀም ከሆነ፣ Streak፣ ሊጉና የቃላት ዝርዝሩ አብረውት ይቀጥላሉ። የመማሪያ ቦታውን አሁን ባለው መለያ ላይ ብቻ ይጨምራል።
ለመጀመር ቢያንስ ስንት ሠራተኞች ያስፈልጋሉ?
በ5 ሠራተኞች ብቻ መጀመር ትችላለህ። Tutoro ለአነስተኛም ሆነ እያደጉ ላሉ ኩባንያዎች ይስማማል።
ውጤት የሚያመጣ የየቀን ልማድ
ለሠራተኞችህ እንግሊዝኛ የሚማሩበት የተሻለ መንገድ ስጣቸው። ለእያንዳንዳቸው የሚስማሙ፣ የሚያስደስቱና በሥራ ቀናቸው መካከል በቀላሉ ጊዜ የሚያገኙላቸው ትምህርቶች።
ጀምር
ለማሳያ ቀጠሮ ያዝ